የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በትውልድ ቅብብሎሽ የተገነባ ኅብረብሔራዊ ሠራዊት ነው - አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

About us                               Contact us                                                Advertisment
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 23/2017 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በትውልድ ቅብብሎሽ የተገነባ ኅብረብሔራዊ ሠራዊትና ተቋም መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። ሀገር አቀፍ 116ኛው የኢትዮጵያ ፖሊስ ቀን የሲምፖዚየም እና አውደ-ርዕይ ዝግጅት "የተለወጠ ፖሊስ፥ እየተለወጠ ላለ ሀገር" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም መከበር ጀምሯል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ የኢትዮጵያ ፖሊስ በትውልድ ቅብብሎሽ የተገነባ ሠራዊትና ተቋም ነው ብለዋል። በተጨማሪም በሀገራዊ ለውጡ ማግስት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ትልልቅ የለውጥ እርምጃዎችን ማስመዝገብ እንደቻለ ገልጸዋል። በሠላምና ደኅንነት ተቋማት የለውጥ እርምጃ ከተወሰደባቸው ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ስኬታማ የማሻሻያ እርምጃ መውሰዱን ተናግረዋል። በዚህም በሠራዊት ግንባታ፣በሰው ሃብት ልማት፣ በዘመናዊ ትጥቅ፣ ወንጀል መከላከልና ምርመራ ገለልተኝነቱን የጠበቀ ህዝባዊ የፖሊስ ተቋም መገንባቱን አንስተዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የኢትዮጵያ፣ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን በማቀፍ ኅብረ-ብሔራዊነቱን የጠበቀ ተቋም ነው ብለዋል። በቀጣይም ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓት እና ሀገራዊ አንድነትን በመጠበቅ፣ በወንጀል መከላከልና ምርመራ፣ በሰብዓዊ መብት ጥበቃና ሕግ የማስከበር ሀገራዊ ኃላፊነቱን በብቃት የመወጣት ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በትውልድ

Comments

  1. Ethiopia Federal police is loyal to the government party

    ReplyDelete

Post a Comment